ለሽብር ተግባር የተዘጋጁ ብዛት ያላቸው የሞባይል ሲም ካርዶችን ከተጠርጣሪው ጋር በቁጥጥር ስር ዋሉ

66

ሐረር ፤ ህዳር 16 ቀን 2014(ኢዜአ) በሐረሪ ክልል ሽብር ተግባር ለማዋል ተዘጋጅተው የነበሩ ብዛት ያላቸው የሞባይል ሲም ካርዶችን ከነተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉ ተገለጸ።

የክልሉ  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ኮሚቴ አባልና በፖሊስ ኮሚሽን  የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የፕላን እና ፕሮጀክት ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ሙሉቀን ዘገየ እንደገለፁት፤ተጠርጣሪው ሲም ካርዶችን ለሽብር  ተግባር ለማዋል ትናንት ምሽት  ይዞ ሲንቀሳቀስ ተደርሶበታል።

በክልሉ ዱክበር አካባቢ  ተደራጅተው አካባቢያቸውን ሲጠበቁ የነበሩ የምሽት የማህበረሰብ የደህንነት ፓትሮል የፖሊስ ተባባሪ አማካኝነት ተጠርጣሪው  እጅ ከፍንጅ መያዙንና  ጉዳዩ በምርመራ ላይ እንደሚገኝ  አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅት የክልሉ ማህበረሰብ ከዕዝ ኮሚቴ እና ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ጸጥታውን ለማስከበር የቁጥጥሩን ስራ አጠናክሮ መቀጠሉንና በዚህም አበረታች ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ኮማንደር ሙሉቀን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም