“አባቶቻችን ድል በነሱበት ወኔ ከመሪያችን ጎን ተሰልፈን ድል እናደርጋለን!”

261

ሚዛን አማን ህዳር 14/2014 (ኢዜአ) “አባቶቻችን ድል በነሱበት ወኔ ከመሪያችን ጎን ተሰልፈን ድል እናደርጋለን!”የሚሉት የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪ አቶ በላይነህ ባቡሬ ናቸው።
 የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪው አቶ በላይነህ ባቡሬ  “አባቶቻችን ድል በነሱበት ወኔ ከመሪያችን ጎን ተሰልፈን ድል እናደርጋለን!” ይላሉ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ግንባር መዝመትን አስመልክቶ ሲጠየቁ ውሳኔያቸው ”የጥንት የአባቶቻችንና የእናቶቻችን ወኔ የተላበሰ ነው”ም ይላሉ።ኢትዮጵያዊነት መታደሱን እያመለከቱ።

በኢትዮጵያውያን ላይ ትልቅ መነቃቃትን የሚፈጥርና ለኢትዮጵያ የሚከፈለውን መስዋዕትነት እንድንከፍል አነሳስቶናል” ሲሉም አክለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ”አድዋን ለመድገም እየተፋለምን ባለንበት በዚህ ወቅት መዝመታቸው የአባቶቻችን ታሪክን ለመድገም ያስችላል” ብለዋል።

ያኔ ኢትዮጵያውያን ለወራሪ ቅኝ ገዢ ኃይል እንዳሸነፉ ሁሉ፤ አሁንም አሸባሪውና ወራሪው ህወሓት እንደሚያሸንፉ በመግለጽ።

ሌላዋ የከተማዋ ነወሪ ወይዘሮ ዝናሽ ሽፈራው ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ለሀገራችን ያለንን ፍቅር በተግባር እንድናሳይ የሚገፋፋ አርዓያነት ያለው ውሳኔ ነው ብለውታል።

”ሀገርን በምቾት ጊዜ ብቻ ሳይሆን፤ በፈተናና ችግር ላይ ሆናም መስዋዕትነት እየከፈሉ መምራት እንደሚያስፈልግ ተረድተናል” ያሉት አስተያየት ሰጪዋ፣”ፈለጋቸውን ተከትለን የሚጠበቅብንን ሁሉ እናደርጋለን” ሲሉም ተናግረዋል።

ሌላው የከተማዋ ነዋሪ አቶ ካሣሁን ከበደ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ውሳኔ ለመከላከያ ሠራዊት ወኔ፣ለሕዝብ ደግሞ መነቃቃት የሚፈጥር ታላቅ ውሳኔ እንደሆነ አመልክተዋል።

ከዚህም ባሻገር ወጣቱ ትውልድ የአገር ፍቅር እንዲሰርጽ ያደርጋል ብለዋል።

ውሳኔያቸው በወርቃማ ቀለም ተጽፎ በኢትዮጵያውያን የሚዘክር ታሪክ እንደሚሆንም አቶ ካሳሁን  አስታውቀዋል።

”ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ለአገርና ለሰንደቅ ዓላማ ያላቸውን ክብር እንዳሳዩ ሁሉ፤ እኛም ተቀራርበን ላለችን አንዲት አገር ነጻነትና ክብር መታገል አለብን” ብለዋል።

ወይዘሮ ራሄል ሌዊ በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአገር ህልውና ለማስከበር ራሳቸው መዝመታቸው ለሌሎች ኢትዮጵያውያን መነሳሳትን በመፍጠር ጠላትን ድል ለመምታት ያስችላል እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

“እኛም በአካባቢያችን የሚዘምቱትን እያበረታታን ስንቅና ሞራል በመለገስ ደጀንነታችን እናጠናክራለን” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ታላቅ ነገር አደረጉም ይላሉ፦

”ኢትዮጵያ ለምዕራባውያን ጫና እጅ የማትሰጥ ጠንካራ ሀገር መሆኗን።”