በኬኒያ የቱሪስት ፍሰት ከፍተኛ መነቃቃት አሳይቷል

113

ህዳር 14 /2014 (ኢዜአ) በኬኒያ ዋነኛ ኤርፖርቶች የሚገቡ አለም አቀፍ ቱሪስቶች ቁጥር በሶስተኛው ሩብ አመት ከአምናው ሲነፃጸር ከፍተኛ ጭማሬ አሳይቷል።

ለቱሪስቶች ቁጥር መጨመር የአገር ውስጥና የአለም አቀፍ ክትባት ሽፋን መጨመሩንም ነው የተነገረው፡፡

ኬኒያ 217,873 ቱሪስቶችን ናይሮቢ በሚገኘው በጆሞ ኬኒያታ አየር ማረፊያና በሞምባሳ ከሃምሌ እስከ መስከረም ተቀብላለች ፤እኤአ በ 2020 በተመሳሳይ ወቅት የጎብኝዎች ቁጥር 36 ሺህ 987 እንደነበር ተገልጿል፡፡

የኬኒያ የቱሪዝም ሚኒስትር ካቢኔት ሴክረተሪ ናጂብ ባላላ እንዳሉት የከኒያ መንግስት በኮቪድ ተፅእኖ ስርም ሆኖ ቱሪዝም ባሳየው መነቃቃት ተበረቷቷል ብለዋል።

ኬኒያ የክትባት አሰጣጡን በማፋጠኗና አንዳንድ ገደቦችንም በማንሳቷ የተገኘ ውጤት መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

የሆቴሎችና የመዝናኛ ማእከላት ገደብ መነሳትም የቱሪዝም ዘርፉን ማነቃቃቱ ታውቋል፡፡

ኬኒያ የተያዘው የፈረንጆች አመት እስከሚያበቃ ለ10 ሚሊየን ሰዎች ክትባቱን ለመስጠት አቅዳለች ፤የሀገሪቱ መንግስት የተወሰኑ ገደቦችን በማንሳትም እኤአ አስክ ህዳር 20 /2021 ክትባቱን ለ6.4 ሚሊየን ዜጎች ክትባት መስጠቷን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም