የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን የአሸባሪው ህወሓትን ሀሰተኛ መረጃ ለማሰራጨትበሱዳን ከትመዋል

207

ህዳር 12 ቀን 2014 (ኢዜአ) “ሲኤን ኤንን ጨምሮ ሌሎች ምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን የአሸባሪው ህወሓትን ሀሰተኛ መረጃ ለማሰራጨት በሱዳን እየተሰባሰቡ ነው” ሲል ኬንያዊው የወንጀል ምርመራና የደህነንት ጉዳዮች ተንታኝ ኮሊንስ ዋንደሪ አስታወቀ።

አሸባሪው ህወሓት የመጨረሻ የሆነውን የውሸት ፕሮፓጋንዳ በቅጥረኛ ምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን በማሰራጨት የለመደውን ህዝብ የማሸበርና ጥርጣሬ የመፍጠር ዘመቻውን ለማካሄድ መዘጋጀቱን የተለያዩ ምንጮች እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

በዚህም ይህው ኬንያዊው ተንታኝ ኮሊንስ ዋንደሪ በትዊተር ገጹ ላይ እንዳሰነበበው፤ የአሸባሪው ህወሓት ደጋፊ ሆነው ኢትዮጵያን በተመለከተ ሀሰተኛ መረጃ እያሰራጩ የሚገኙት ቢቢሲ፣ ሲኤንኤን፣ ሮይተርስ፣ አሶሼትድ ፕሬስ፣ አልጀዚራ፣ ቴሌግራፍ፣ ፍራንስ 24 እና ሌሎች ምእራባዊያን መገናኛ ብዙሃን አሸባሪው ህወሓትን በመደገፍ ሀሰተኛ መረጃዎችን ለማሰራጨት በሱዳን ገዳሪፍ ግዛት እየተሰባሰቡ መሆኑን አጋልጧል።

መገናኛ ብዙሃኑ በሱዳን ገዳሪፍ ግዛት ዋድ ሙዛሚል በተባለችው ከተማ መሰባሰባቸውን ነው ያጋለጠው፡፡በቅርቡም ለቢቢሲ፣ ሲኤን ኤን፣ ሮይተርስና አሶሼትድፕሬስ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት፣ የኢትዮጵያን እውነታ አዛብተው በመዘገብ፣ ሚዛናዊና ሙያዊ ያልሆነ መረጃ በማሰራጨት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ይታወሳል።