የአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ልዩ መልእክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አዲስ አበባ ገብተዋል።

113

ኦባሳንጆ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በመገናኘት፣ የሰላም መፍትሔ በማፈላለግ ሂደታቸው የደረሱበትን ሐሳብ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያብራሩ ሲሆን በተጨማሪም በሰብአዊ ርዳታ ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

ኦባሳንጆ በቆይታቸው መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአፍሪካ ኅብረት አምባሳደሮች በኢትዮጵያ ጉዳይ እስካሁን በደረሱባቸው ነጥቦች ዙሪያ ማብራሪያ እንደሚሰጡ የደረሰን መረጃ ያመለክታል ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም