አሸባሪው ህወሐት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያደረገው ተግባር ቅዠት ሆኖ ቀርቷል

ህዳር 8 / 2014 (ኢዜአ) አሸባሪው ህወሃት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያደረገው ተግባር ቅዠት ሆኖ ቀርቷል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ቦሌ ክፍለ ከተማ ለመከላከያ ሰራዊት በአይነትና በገንዘብ ከ90 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል።

በህልውና ዘመቻ ሰራዊቱን ለሚቀላቀሉ ዘመች ወጣቶችና የቀድሞ ሰራዊት አባላት ሽኝት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በመርሃ-ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ የክፈለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አለምፀሐይ ሽፈራውን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ጊዜ ኢትዮጵያ በደምና አጥንት የተገነባች እና የማትፈርስ መሆኗን ጀግኖች ልጆቿ አረጋግጠዋል ብለዋል፡፡

ከአሸባሪው በተጨማሪ የተለያዩ ኃይሎች ኢትዮጵያን ለማፍረስ ቢንቀሳቀሱም አልተሳካላቸውም ሲሉም ጠቁመዋል፡፡

ዘማቾች አሸባሪውን እንደሚቀብሩ ጥርጥር የለንም ብለዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች የከተማው ነዋሪ ኢትዮጵያን ለመጠበቅ እያደረገ ላለው ተግባር አመስግነዋል፡፡

የአገሪቱን የግዛት አንድነት ለማናጋትና የአገሪቱን ህልውና ለማፍረስ እየተደረገ ያለው ሴራ ህልም ሆኗልም ብለዋል፡፡

የከፍለ ከተማው ነዋሪዎች በአይነትና በገንዘብ ከ90 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸውን የቦሌ ክፍለ ከተማ ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ አለምፀይ ሽፈራው ገልፀዋል፡፡

ህብረተሰቡ አሸባሪ ህወሐትን የመደምሰስ እና የአካባቢውን ሰላም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል፡፡

-አካባቢህን ጠብቅ

_ ወደ ግንባር ዝመት

_ መከላከያን ደግፍ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም