ሲ.ኤን.ኤን ሰራተኞቹን ሊያባርር ነው

727

ህዳር 5/2014 (ኢዜአ) የአሜሪካው ኬብል ኒውስ ኔትዎርክ (CNN) በተመልካች ድርቅ መመታቱን ተከትሎ በርካታ ሰራተኞቹን ሊያሰናብት ነው ተባለ።

ኢትዮጵያ ላይ ተደጋጋሚ ሀሰተኛ ዜናዎችን በማሰራጨት የተጠመደው ሲ.ኤን.ኤን ባለፈው ጥቅምት ለአየር ካቀበቃቸው ስርጭቶች መካከል አንዳቸውም ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተመልካች ሳያገኙ ቀርተዋል።

ለወትሮው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተመልካቾች የነበሩት ሲ.ኤን.ኤን ዘገባዎች አሁን ላይ ተመራጭ እየሆኑ አይደለም።

በደረጃ ሰንጠረዡ የተስተዋለው የተመልካቾች ቁጥር ማሽቆልቆልም ከፍተኛ ድንጋጤ መፍጠሩን ነው ዘገባዎች የሚያመላክቱት።

ይህን ተከትሎ ሲ.ኤን.ኤን በርካታ ሰራተኞቹን ከሥራ ሊያባርር እንደሆነ ነው የተሰማው።

የምዕራባውያን የመገናኛ ብዙኃን በሚያሰራጯቸው ሀሰተኛና የፈጠራ ትርክቶች ምክንያት ተአማኒነታቸው ጥያቄ ውስጥ እየገባ መምጣቱን ነው የመስኩ ተንታኞች የሚገልጹት።