የኢድ አል አድሃ በዓልን ስናከብር አቅመ ደካሞችን በመደገፍና የተቸገሩትን በመርዳት ልናሳልፍ ይገባል --የእምነቱ ተከታዮች

51
አዲስ አበባ ነሀሴ 14/2010 የእስልምና እምነት ተከታዮች የኢድ አል አድሃ በዓልን ሲያከብሩ አቅመ ደካሞችን በመደገፍና የተቸገሩትን በመርዳት ሊያሳልፉ እንደሚገባ የእምነቱ ተከታዮች ጠየቁ። ኢዜአ ያነጋገራቸው የእምነቱ ተከታዮች እንዳሉት ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር ከአቅመ ደካሞችና ከተቸገሩ ሰዎች ጋር አብሮ በመብላት መሆን አለበት ብለዋል። አብሮ መብላት ኢትዮጵያዊ ባህል በመሆኑ በሰላም፣ በፍቅርና በአንድነት ሆኖ ከደካሞች፣ ወላጅ አልባ ከሆኑ ልጆችና ከአካል ጉዳተኞች ጋር በጋራ ማክበር እንደሚገባም ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የተጀመረውን የፍቅር ጉዞ  ለማጠናከርም በዓላትን ብቻ ጠብቆ ከመረዳዳት ይልቅ ዘወትር የተቸገሩ ሰዎችን መርዳትና አብሮ የመብላት ባህሉ ማጠናከር  ይገባል ብለዋል። ወጣት  ነቢላት  አብራር የተባለ የእምነቱ ተከታይ በሰጡት አስተያየት" ባህሉን ስናከብር ያለው ከሌለው ጋር ተካፍሎ ያው የቲም ልጆች ሊኖሩ ይችላሉ፣ በየመስጂዱ ደግሞ ፣ አካል ጉዳተኞች ሊኖሩ ይችላሉ  ከነሱ ጋር ሼር በማድረግ ማለት ነው ተካፍለን በመብላት ነው የምናሳልፈው  መሆን አለብት˝ ብለዋል "እኛ ባህሉን በተመለከተ  ድሮም ከሌለው ሰው ጋር ያለችንን ተባብረን ተካፍለን  ለመብላትና በደስታ ለማሳለፍ ለማብላትና ለማልበስ ችግርተኛ አይተን ማለፍም አንችልም''  በማት የተናገሩት የእምነቱ ተከታይ አቶ ሱልጣን ፋሪስ  ናቸው፡፡ በመላው ዓለም የሚከበረው 1 ሺህ 439 ዓመተ ሂጅራ የኢድ አል አድሃ በዓል በነገው ዕለተ በአዲስ አበባ ስታዲዮም እና በክልሎችም በድምቀት ይከበራል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም