በሀዋሳ ጀግናው መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍና የአሸባሪው ህወሀትና ሌሎች አፍራሽ አላማ ያላቸው ኃይሎችን እኩይ ተግባር የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

97

ጥቅምት 29 ቀን 2014 (ኢዜአ)በሀዋሳ ከተማ ጀግናው መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍና የአሸባሪው ህወሀትና ሌሎች አፍራሽ አላማ ያላቸው ኃይሎችን እኩይ ተግባር የሚያወግዝ ክልል አቀፍ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው ፡፡

በህዝባዊ ሰልፉ ላይ በግንባር ለእናት ሀገሩ ክብርና ኩራት እየተዋደቀ ለሚገኘው ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የፀጥታ ኃይሎች አለኝታነትና አጋርነትን የሚገልፁ እንዲሁም አሸባሪው ህወሀት ፡ ሸኔና አፍራሽ አላማ ያላቸው የውጭ ጠላቶች ሀገር ለማፍረስ እየፈፀሙ ያሉትን እኩይ ተግባር የሚየወግዙ መልእክቶች እየተላለፉ ይገኛሉ ፡፡

ሰልፈኞቹ " እኛ ሲዳማዎች ለማንኛውም ሀገራዊ ጥሪ በግንባር ቀደምትነት እንሰለፋለን " " ከፋፋይና ሀገር አፍራሽ ሀይሎችን ከኢትዮጵያ ጠራርገን ለማስወገድ ቆርጠን ተነስተናል " " ከጀግናው መከላከያ ሰራዊትና ከመላው የፀጥታ ሀይሎች ጎን ነን " የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችን እያስተላለፉ ነው ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም