ማሸነፍ ግድ ነው፤ ለምን?

327

የኢትዮጵያ ጠላቶች አገራችንን የማፈራረስና ስሟን ከምድረ ገጽ የማጥፋት ውሳኔያቸውን ከያሉበት ተሰባስበው በምድረ አሜሪካ በፊርማቸው ይፋ አድርገዋል። ከየትም የተሰባሰቡና የኢትዮጵያን ህልውና አደጋ ላይ የመጣል ተልዕኮ ያላቸው በምድረ አሜሪካ የተቀምጡ ግለሰቦች ፊርማቸውን በማኖር ዱለታቸውን አሳውቀውናል። በህዝብ የተመረጠውን የኢትዮጵያን መንግስት “በሀይል ወይም በድርድር እናፈርሰዋለን። አገሪቷ የመከላከያ ሃይል የላትም” ሲሉም ተደምጠዋል።

መንግስት ኢትዮጵያን ለማፍረስ “ከውስጥና ከውጭ ጠላቶቻችን እየተረባረቡብን ነው” ለሚለው ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው። አሜሪካ አሻንጉሊት መንግስት የመመስረት ህልሟን እውን እንዲያደርጉላት ያሰበሰበቻቸው ግለሰቦችና የሽብርተኛ ቡድን አባላት ከራሳቸው ጥቅም እጅግ የራቀ ሀሳብ እንደሌላቸው አሳይተውናል። አሁን በጥንቃቄ ካስተዋልነው ከውጭና ከውስጥ ሃይላት ጋር የሚደረገው ትንቅንቅ ጫፍ በደረሱን ያረጋግጣል።

በሀሰት ወሬ ህዘብ እነዲሸበር ማድረግ፣ በኢኮኖሚያዊ ማዕቀብና ዲፕሎማሲያዊ ተግዳሮት ጫናወን ማጠንከር፣ በሰብዓዊ መብት አመካኝቶ ለሽብርተኛ የሚሰጠው ድጋፍ የኢትዮጵያዊያንነ አንድነት ማጠነከሩና አልበገርም ማለቱ ተስተውላል። አሁን የከፋውን የመጫረሻውን አቅም ሁሉ ለመጠቀም አሜሪካ ከአሸባሪው ህወሃት ጎን መቆሟን በግልጽ አሳይታለች። ጥቂት ተላላኪዎችን አደራጅታ ለቀጣይ እርምጃዋ ምቹ መደላድል እየፈጠረች ነውመ ብሎ ማሰበ ይቻላል። ይህን ካስተዋል አሁን የአሸባሪውን ህወሃት ታጣቂ የመደንምሰስና ጦርነተን በአሸናፊነት  የማጠናቀቅ ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠውና የግድ መሆን እንዳለበት ግልጽ ነው። ጠላታችንን በብርቱ ክንድ ማሸነፍ  የግድ ነው።

ማሸነፍ ግድ የሆነው ለምንድን ነው? ለምን? ለምን? የሚለውን እያንዳንዳችን መጠየቅ ይኖርብናል። ግድ ማሸነፍ ያለብን በጠላት በተያዙ አካባቢዎች ያሉ ዜጎቻችን ጥቃታቸውና ርሃባቸው ስለተሰማን? በጠላት እጅ በወደቁ አካባቢዎች ሴቶችና ወንዶች ስለተደፈሩ፣ አዛውንቶች ክብራቸው ተገፎ ቄሶችና ሼሆች ተዋረደው በአደባባይ ስለተረሸኑ፣ የአርሶ አደሩ ሀብት የሆኑትና ጠላትና ወዳጅ መለየት የማይችሉት እንስሳት በጥይት ሩመታ ስለተገደሉ ነው ማሸነፍ የግድ የሆነብን? ወይስ ሌላ ጥልቅ ምክንያት ስላለን? ይህን በጥንቃቄ ማየት ያስፈልጋል።

እነዚህ ሁሉ ጠላትን ለመግጠምና ለማሸነፍ ሊጠቀሱ የሚችሉ ምክንያቶች ናቸው። ቁጭት አድሮብን ለመጥቀስ እንችላለን። በጥልቀት ስንመረምረው ግን አሁንም ለምን? ለሚለው ጥያቄ በቂ ምላሽ አይሰጠንም። ከዚህ በላይ ከፍ ያለ ጥልቅ ምክንያት አለን። ገና ከመጀመሪያው ጀምሮ መንግስት ሲነግረን፣ በየአካባቢው ያለህዝብ ሲያወራን የነበረ ኢትዮጵያን የማፍረስና ኢትዮጵያዊነትን የማጥፋት አገር አልባ ዜጎች እንድንሆን የተሸረበውን ሴራ በጣጥሶ የማለፍ ታለቅ ምክንያት አለን።

ጠላታችን አሸባሪው ህወሃት ለዘመናት ተከብሮ የኖረውን ነጻነታችንን ሊሸጥ የተደራደረ ስብስብ ነው። ጠላታችን ለአፍሪካ ኩራት፣ ለጥቁሮች የነጻነት ቀንዲል የሆነውን የአድዋ ታሪካችንን ከምድረ ገጽ ሊያጠፋ የቆመ ሃይል ነው። በዘመናት ውስጥ ድንቅ ታሪክ ያስመዘገበች፣ ስሟ በወርቃማ ቀለም በድል አድራጊነት የተመዘገበውን ኢትዮጵያ  የማጥፋት ሴራ የመጨረሻው ሙከራ እየተደረገበት ያለ ጊዜ መሆኑ ነው።

አሸባሪው ህወሃት ኢትዮጵያን እንድትፈርስ ትንሽ አገር እንድትሆን ሙከራ ያደረገው ዛሬ ሳይሆን ለሲያድባሬ መንግስት የድጋፍ እጁን ከሰጠ ጊዜ አንስቶ ነው። ኢትዮጵያን ለወረረ ሃይል ድጋፍ በማድረግ የክህደቱን መጨረሻ አሳይቷል፤ ዛሬ አገራችንን ለማጥፋት ከተነሱ ሃይሎቸ ጋር መስራቱ አዲስ አለመሆኑን ያመላክታለ። ይህ ስብስብ  ባርነትን የተለማመደ፣ ተላላኪነትን አሜን ብሎ የተቀበለ የጥፋት መልዕክተኛ እስካልጠፋ ድረስ አገርን አሳልፎ መስጠትና መሸጥ አያቆምም። ለዚህም ነው በፍጥነት መደምሰስ አለበት የምንለው።

አሸባሪው ህወሃት አገር የማስተዳደር እድል ባገኘበት ዘመን ከእርሱ የተሻለ ሀሳብ ያላቸውን አንድም በማሳደድ፣ ሊላ ጊዜ በመግደልና በማሰር አገሪቷን እወቀት አልባ ያደረገ ሃይል ነው። የሚያስቡና የሚያሰላስሉ ሰዎችን በተለያየ መንገድ እያጠፋ፣ እስር ቤት አያሰቃ መቆየቱ የአደባባይ ምስጢር ነው።  ይህ ሃይል ዳግም የዚህ ዓይነት ግፍ አንዲፈጽም የሚፈቅድ ከሰማይ በታች ምንም ሃይል ሊኖር አይገባም፤ አይችልም። ለዚህም ነው ጦርነቱን ማሸነፍ ያለብን።

ጠላታችን ያመኑትን ሲከዳ፣ ያመኑትን ሲያጠቃና በስቃያቸው ሲደሰት የአሸናፊነት ቀረርቶ የሚነፋ እንጥፍጣፊ የጀግና ባህሪ የሌለው ከሃዲ ሃይል ነው። ለዚህ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የፈጸመው ዘግናኝ ጭፍጨፋ በአብነት መጥቀስ ይቻላል። ክፉውን ሁሉ አብረን አሳልፈናል፤ ጠላታችንን ተጋፍጠን አንዳችን ስነወድቅ ሌላችን ደግፈናል በሚል እምነት ከወንድሙ አጠገብ የተኛ የመሰለውን ሰራዊት በጥይት በመጨፈጨፍ “መብረቃዊ እርምጃ” መውሰዱን ለማውራት ያልዘገነነው ፍጹም ገፈኛ ጠላት ነው። ነገ በእያንዳንዳችን ላይ ከማድረግ ወደ ኋላ የማይል ዘላለማዊ ጠላት ነውና ከምድረ ገጽ መጥፋት አለበት።

አገር በመራበት ዘመን ይፈጽመው የነበረወን ወሲባዊ ጥቃት ያስፋፋ፣ ከኢትዮጵያዊነት ክብረና ሞገስ የተነሳ ለመጻፍም ሆነ ለመናገር የሚቀፈን ድርጊት በሴቶችም ሆነ በወንዶች ላይ የፈጸመ “ሰይጣን የሚቀናበት” ቡድን ነውና መወገድ ይኖርበታል። ፍጹም ጊዜ ሊሰጠው የማይገባ ሃይል ነው። ማሸነፍ ግድ የሚለንም ዳግም በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የመከራ ዘር እንዳይዘራ፣ የግፍና የካኔ ጥግን እንዳናይ ነው።

ይህን ጠላት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማሸነፍ ኢትዮጰያዊያን መነሳታቸው ታላቅነታቸው፣ ሰብዓዊ ክብራቸውነና የነጻነት ቀናኢነታቸውነ ያሳያል። ለማሸነፍ ግን ጊዜ መስጠት አያስፈልግም። ጠላታችን ሰላማችን ወስዶብናል። ክብራችንን ተፈታትኖታል። ነጻነታችንን ግን በፍጹም፤ በፍጹም፤ በፍጹም ሊወስደው ቀርቶ ሊያስበው እንደላይችል ማሳየት አለብን። ለዚህ ደግሞ ጊዜ የለንም። ለበኋላ የምንለው ምንም የተረፈን ሽርፍራፊ ሰከንድ የለንም። ዛሬ፤ አሁን ለማሸነፍ መተመም አለብን።