የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

129
አዲስ አበባ ሰኔ 14/2010 የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል። የኢህአዴግ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት የህዝብና የውጭ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሳዳት ናሻ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የግንባሩ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ስብሰባውን ሲያጠናቅቅ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ  ከዚህ ቀደም ግንቦት 28 ቀን 2010 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ትልልቅ ውሳኔዎችን ማሳለፉ ይታወሳል። ካሳለፋቸው ውሳኔዎች ውስጥ የዕድገት ደረጃ ጋር የሚመጣጠን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎችን ለመውሰድ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥና በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ለዓመታት ተፈጠጥሮ የቆየው አለመግባባት እንዲረግብና ወደ ዘላቂ ሰላም እንዲመለስ የተላለፈው ውሳኔ ትልቅ ውጤት እንዳመጣ ይታወቃል። ከኢኮኖሚ ማሻሻያዎቹ መካከል የአገር ውስጥ ባለሃብቶች በሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ የአክስዮን ድርሻ እንዲኖራቸው የሚያስችለው ውሳኔ ተጠቃሽ ነው። ግንባሩ ባስቀመጠው አቅጣጫ አገሪቱ ከኤርትራ ጋር የነበራት ግንኙነት መልኩን ቀይሮ ጠንካራ ወዳጅነት መመስረት አስችሏል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተመራ ልዑክ ወደ ኤርትራ በማቅናት ባደረገው የስራ ጉብኝት ለአመታት የዘለቀውን የሻከረ ግንኙነት ወደሰላማዊ ግንኙነት መቀየር ማስቻሉ ይታወቃል። የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ የሶስት ቀናት የስራ ጉብኝት በማድረግ በቀጣይ በሁሉም ዘርፍ መስራት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ሊፈጠር ችሏል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም