ቻይና ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በትበብር በመስራት ታምናለች

54

ጥቅምት 25 ቀን 2014 (ኢዜአ) ቻይና ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በወጪ ንግድ፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመከላከልና በሌሎች አለም አቀፍ ግንኙነቶች በትብብር በመስራት እንደምታምን የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንቱ አራተኛው የቻይና አለም አቀፍ የገቢ ኤክስፖንና ሆንጋኩዋ አለምአቀፍ ኢኮኖሚክ ፎረምን አስመልክቶ በቪዲዮ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ጂንፒንግ በመልእክታቸው ኤክስፖውን ለመሳተፍ የተገኙትን ሁሉ በቻይና መንግስትና መንግስትና ህዝብ ስም አመስግነዋል።“አሁን ያለንበት ጊዜ አለምአቀፍ ትብብርን ይሻል” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ቻይና አለም አቀፍ ንግድ በተለይ የኢንዱስትሪ ሰንሰለቱን ጠብቆና የተረጋጋ ሆኖ እንዲቀጥል እንደምትሰራ አረጋግጠዋል።

“ቻይና በተለይ ኮቪድ-19 በአለም አቀፉ ንግድና ቱሪዝም ላይ ያሳደረውን ተፅእኖ ትረዳለች” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ተጽእኖውን ለመቀነስ የተለያዩ ድጋፎችን ስታበረክት መቆየቷን አውስተዋል፡፡

350 ሚሊዮን የአፍና የአፍ መሸፈኛማስክ፣ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶዝ ክትባት፣ የመመርመሪያ መሳሪያችንና ሌሎችም የመከላከያ ቁሶችን ስታበረክት መቆየቷን ለአብነት አንስተዋል፡፡

ቻይና የወጪ ንግድን፣ ፈጠራን፣ ቱሪዝምን፣ የኢንቨስትመንትና የንግድ እድሎችን በማበረታታት አለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት ትወጣለች፤ በተለይም በታዳጊ ሀገራት የወጪ ንግድ እንዲበረታታም ትሰራለች ሲሉ አክለዋል፡፡ኤክስፖው እ.አ.ኤአ ከህዳር 5 እስከ 10 ቀን 2021 የሚካሄድ ሲሆን ከ127 ሀገራት 3 ሺህ የንግድ ተቋማት እንደሚሳተፉበት የዥንዋ ዘገባ አመልክቷል።

ኢትዮጵያ በኤክስፖው በተለይ በቡና ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብቶች እንደሚሳተፉ የቡናና ሻይ በላስልጣን ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ኤክስፖው ለቡና ወጪ ንግድ ማደግ ዕድል ይዞ መምጣቱም ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም