በ2 ነጥብ6 ቢሊዮብን ብር ወጪ የተገነባው የረጲ የደረቅ ቆሻሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ እየተመረቀ ነው

98
አዲስ አበባ 13/2010 በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው ረጲ የደረቅ ቆሻሻ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት የምረቃ ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው፡፡ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር እንደሆነ ታውቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ከተለያዩ አለም አገሮች የመጡ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ ከአምስት አመት በፊት በ2006 ዓ ም ግንባታው የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት በአመት በአማካይ 185 ጊጋ ዋት ያመነጫል፡፡ ሀይል ለማመንጨት በቀን 1 ሺህ 400 ቶን ደረቅ ቆሻሻ በግብዓትነት ይጠቀማል፡፡ የፕሮጀክቱ ሙሉ ወጪ በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ነው፡፡ ስራውን ያከናወነው ካምብሪጅ ኢንዱስትሪ ሃላፊነቱ የተወሰነ ሲሆን በንዑስ ተቋራጭነት የቻይናው ኤሌክትሪክ ኢንጂነሪንግ ሊሚትድ (CNEEC) ነው፡፡ በፕሮጀክቱ ግንባታ ላይ 1 ሺህ 300 ኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ የስራ እድል የተፈጠረላቸው ሲሆን፤ 286 የውጭ አገር ዜጎችም ተሳትፈውበታል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም