ደሴ ከተማ የተፈጠረው መጠነኛ አለመረጋጋት ተስተካክሎ ማህበረሰቡ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው እየተመለሰ ነው

300

ጥቅምት 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) ደሴ ከተማ ውስጥ ተፈጥሮ የነበረው መጠነኛ አለመረጋጋት ተስተካክሎ ማህበረሰቡ ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው እየተመለሰ ነው።

ትናንት ከሰዓት አካባቢ የአሸባሪው ህወሃት የጥፋት ተላላኪዎች በከተማዋ ውስጥ በፈጠሩት የተለመደ የውሸት ውዥንብር መጠነኛ አለመረጋጋተት ተስተውሎ ነበር።

የከተማዋ ወጣቶች የአሸባሪውን ህወሃት የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ቀድመው በመረዳታቸው ‘ከተማችንን ለቀን የትም አንሄድም’ በሚል ባደረጉት እንቅስቃሴ ነዋሪውን ማረጋጋት ችለዋል።

ወጣቶቹ በከተማዋ መጠነኛ አመረጋጋት እንዲፈጠር ምክንያት የሆኑ የአሸባሪው ህወሃት የጥፋት መልዕክተኞችን ከማህበረሰቡ ውስጥ ለይተው በማውጣት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርገዋል።

‘ደሴ ከተማን መቆጣጠር ጀምረናል’ ብሎ በቦሩ ሜዳ አቅጣጫ መጥቶ የነበረው ወራሪ ኃይል በአገር መከላከያ ሰራዊት፣ በአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚሊሻ የተቀናጀ ክንድ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ እየተደመሰሰ፣ እጅ እየሰጠ እና እግሬ አውጭኝ እያለ ሽሽቱን ተያይዞታል።

በጦሳ ተራራ በመሹለክለክ ሰርጎ በመግባት የደሴ ከተማና አካባቢዋን ማህበረሰብ ለማሸበር ሞክሮ የነበረው የወራሪም ሙሉ በሙሉ ተመትቷል።

በወሎ ግንባር የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚሊሻ የወገን ጦር ፍጹም የበላይነት ታላቅ ጀብዱና ድል እየተቀዳጁ ይገኛል።

የወራሪው ሽብርተኛ ኃይልም ፍርክስክሱ ወጥቶ አምስትም አስርም እየሆነ ማህበረሰብን ከማሸበር ውጭ ወሎና አካባቢዋን ተሻግሮ አገርን ለማፍረስ የያዘው ህልም አከርካሪው ተሰብሮ ምንም ማድረግ የማይችል ተልፈስፋሽ ኃይል ሆኖ ነው ያለው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም