የፌዴራልና ክልል መንግሥታት የህግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ነው

253

ባህርዳር፤ ጥቅምት 19/2014 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በተገኙበት የፌዴራልና ክልል መንግሥታት የህግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

የምክክር መድረኩ  የኢፌዴሪ የመንግሥታት ግንኙነት ስርዓትን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1231/2013 መሰረት የሚካሄድ መሆኑ ተመልክቷል።

የፌዴራልና  ክልል መንግሥታት የህግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ የህዝብ የጋራ ጥቅም ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊዎቹ እንደሚመክሩ  ይጠበቃል።

በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በዝርዝር በመምከር የተለያዩ ውሳኔዎችንና የስራ አቅጣጫዎች እንደሚተላለፉም እንዲሁ።

የፌደራል መንግስት ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ጋር በቅርበት ለመስራት መድረኩ እንደሚያስችልም ተመልክቷል።

በመድረኩ የሁሉም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች፣  የአዲስ አበባና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች ፣ ሌሎችም የፌዴራል እና ክልል የበላይ አመራሮች በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።