ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ የብሔራዊ ስታዲየም የግንባታ ሂደትን ጎበኙ

193

ጥቅምት 14 ቀን 2014 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የብሔራዊ ስታዲየም የግንባታ ሂደትን ጎበኙ።

በጉብኝቱ ወቅት አጠቃላይ የስታዲየሙ ግንባታ ሂደት ያለበት ሁኔታ እና ያጋጠሙ ችግሮች በተመለከተ በአማካሪ ድርጅቱ እና የግንባታውን ሂደቱን በሚከታተሉት አካላት ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

ከገለጻው በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስታዲየሙ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ያጋጠሙ ችግሮችን መንግስት እንደሚፈታ ገልፀዋል።ግንባታው በአጭር ጊዜ ጥራቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ እና ለአገልግሎት ዝግጁ እንዲሆን የስራ መመሪያም ሰጥተዋል።