መቱ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው

85

መቱ ፣ጥቅምት 13/2014 (ኢዜአ) የመቱ ዩኒቨርሲቲ በጤና ትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።

ዩኒቨርሲቲው እያስመረቀ ያለው በጤና ሳይንስ ኮሌጁ በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን 444 ተማሪዎችን ነው።

ከተመራቂዎቹ  370 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ቀሪዎቹ የሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 143 ሴቶች እንደሆኑ ተመልክቷል።

በምረቃ ሥነ- ሥርዓቱ ላይ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር  ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ነፃነት ወርቅነህ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም