በመቀሌ አሸባሪው የህወሃት ቡድን ለወታደራዊ ማሰልጠኛነት ሲጠቀምበት የነበረው ቦታ ዛሬ የአየር ጥቃት ኢላማ ሆኗል

279

ጥቅምት 12/2014(ኢዜአ) በመቀሌ አሸባሪው የህወሃት ቡድን ለወታደራዊ ማሰልጠኛነት ሲጠቀምበት የነበረው ቦታ ዛሬ የአየር ጥቃት ኢላማ መሆኑን የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል።

ከስልጠና ባሻገር የሽብር ቡድኑ ቦታውን የወታደራዊና መገናኛና ማዘዣ ማዕከሉ አድርጎ ሲጠቀምበት እንደቆየም ተገልጿል።

ማዕከል ለአሸባሪው ቡድን ወታደራዊ ሥልጠና ከመዋሉ በፊት የኢፌዴሪ መከላከያ ማሠልጠኛ ማዕከል እንደነበረው ታውቋል።

የመከላከያ ሠራዊቱ የአየር ድብደባዎች ዒላማ ያደረጉት የአሸባሪው ህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ፣ማከማቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎችን ብቻ መሆኑም ተገልጿል።

በተለይም የሽብር ቡድኑ የመስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ ኩባንያን የከባድ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ፤ ማምረቻ ፤እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያ አድርጎ ሲጠቀምበት እንደነበር ከቀናት በፊት መዘገባችን ይታወሳል።