የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ በመፍጠር የስራ አጥነት ችግርን ለማቃለል ይሰራል

78

ጥቅምት 12 ቀን 2014 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ በመፍጠር የስራ አጥነት እና የኑሮ ወድነት ችግርን ለማቃለል የሚሰራ መሆኑን የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል ተናገሩ።
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች በቀጣይ በሚያከናወኑት ስራ ላይ በማተኮር ውይይት እያደረጉ ነው።

በመርሃ ገበሩ ላይ መልአክት ያስተላለፉት የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል በኢትዮጵያ የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ በመፍጠር የስራ አጥነት እና የኑሮ ወድነት ችግርን ለማቃለል በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መስኮች ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰራም ነው ያተናገሩት።

በተለይ የስራ አጥነትን ችግር ለማቃለል እና ዜጎች ባላቸው ክህሎት በየትኛውም የአገሪቱ አካባቢ በመሰማራት ውጤታማ ስራ እንዲያከናውኑ ይደረጋል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ በእውቀትና ክህሎት ተወዳዳሪ እንዲሁም ምርታማ የሰው ኃይል ለመፍጠር የቀጣይ ዋነኛ ትኩረት ይሆናል ነው ያሉት ሚኒስትሯ።

የስራ አጥነትን ችግር በማቃለል እና እየተባባሰ የመጣውን የኑሮውድነት ችግር ለመፍታት አዳዲስ አሰራሮችን መፍጠር እንዲሁም ከተለያዩ ባለደርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

የኢንዱስትሪ ሰላምን ለማረጋገጥ በአሰሪና ሰራተኞች መካከል ሁለቱንም ተጠቃሚ የሚያደርጉ አሰራሮች መፍጠር እነደሚያስፈለገም ጠቁመዋል።