አሸባሪው ህወሃት በንጹሐን ላይ እያደረሰ ያለውንጭፍጨፋ እናወግዛለን…የትግራይ ተወላጆች

339

ሰመራ ፤ ጥቀምት 11/2014 (ኢዜአ)፡ የህወሃት የሽብር ቡድን በአፋር ንጹሃን አርብቶ አደሮች ላይ እያደረሰ ያለውን ጭፍጨፋ እንደሚያወግዙ በአፋር ከልል የሎግያ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ገለጹ።
በአፋር ንጹሃን አርብቶ አደሮች ላይ አሸባሪው ህወሃት እያደረገ ያለዉን ጭፍጨፋ እንደሚያወግዙ በአፋር ከልል የሎግያ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ገለጹ

የሽብር ቡድኑ በንጹሐን ላይ የሚደርሰውን ግፍና ጭፍጨፋ የሚያወግዙ ሰልፎች በክልል የተለያዩ ከተሞች ተካሒደዋል።

የሎግያ ከተማ ነዋሪ አቶ ካላዩ መለስ በተለይ ለኢዜአ እንደተናገሩት አሸባሪው ህወሃት በከፈተዉ ጦርነት በአማራና አፋር ከልሎች ንጹሃንን ኢላማ ያደረገ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀዉስ እያደረሰ ነው።

በተጨማሪም ቡድኑ የተወሰኑ ግለሰቦች የስልጣን ጥም ለማርካት የትግራይን ህዝብም ለአስከፊ ረሃብና ለጦርነት እያዳረገዉ ይገኛል” ብለዋል ።

በተለይም ቡድኑ በአፋር ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በፈጸመዉ ወረራ የአከባድ መሳሪያ ድብደባ ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ ንጹሃን በግፍ መገደላቸዉ እንዳሳዘናቸዉም ተናግረዋል።

ድርጊቱንም ከሰብአዊነት ያፈነገጠ የግፍ ተግባር በመሆኑ አጥብቀዉ እንደሚያወግዙት ገልጸው ከክልሉ መንግስትና ህዝብ ጎን ቁመዉ የሚጠበቅባቸዉን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸዉን ተናግረዋል።

ሌላዉ የሎግያ ከተማ ነዋሪ አቶ ሃይላይ ተስፋየ በበኩላቸዉ የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ወንድም የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ተዛምዶና ተዋልዶ በፍቅርና በሰላም የሚኖር ጨዋ ህዝብ ነዉ

“ይሁንና የህወሀት የህሽብር ቡድን ቁንጮ አመራሮች ሰልጣናቸዉን ለማስከበር ህዝቡ ከሌሎች ወንድም አማራና አፋር ህዝብ ጋር አጋጭተዉ ደም ለማቃባት በመሞከር የግል ፍላጎታቸዉ መጠሚያ እያደርጉት ነዉ”ብለዋል

የሠመራ ከተማ ነዋሪዉ አቶ ሀዱሽ አብርሃ የሽብር ቡድኑ የከፈተው ጦርነት ንጹሃኑን ለስደትና ሞት ከመዳረጉም ባለፈ በተለያዩ አካባቢዎችም መሠረተ ልማቶችን እያወደመ መሆኑ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።

“በወረራ በያዛቸዉ የአፋርና አማራ ክልሎች በንጹሃን ዜጎች ላይ ሆን ተብሎ እየተደረገ የሚገኘዉ የግፍ ግድያ የጨዋዉን የትግራይን ህዝብ እሴቶች የሚቃረን መሆኑን የሚያሳይ ነዉ” ብለዋል።

በመሆኑም በቡድኑ አፋርን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የተደረጉ የግፍ ግድያዎች አጥብቀዉ እንደሚያወግዙ በሠላማዊ ሠልፍ ለመገለጽ በሠመራ ከተማ መገኘታቸዉን ገልጸዋል።

ሌላዉ የሎግያ ከተማ ነዋሪ አቶ ሀይለ ግደይ በበኩላቸዉ በተሠማሩበት የሆቴል ድርጅት ህገ-ወጦችን ከመቆጣጠር ባለፈ ከአካባቢያቸዉ የጸጥታ መዋቅር ጋር ተቀራርበው በመስራት ሰላም እዲረጋገጥ የበኩላቸዉን እየተወጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የአሸባሪውን ወረራ ለመቀልበስ እንደዜጋ ለሠራዊቱና ለክልሉ ልዩ ሃይል የሚጠበቅባቸዉን አስተዋጽኦ በገንዘብና በሞራል በመደገፍ ሀገር የማዳን የዜግነት ግዴታቸዉን እየተወጡ እንደሚገኙም  አስረድተዋል።

በተጨማሪም የሽብር ቡድኑ በተለያዩ አካባቢዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ እየተፈጸመ የሚገኘዉን የግፍ ግድያና ጦርነት ለማዉገዝም ዛሬ በሰልፉ ላይ ተገኝተዉ ድምጻቸዉን ማሰማታቸዉን ገልጸዋል።

በአፋርና አማራ ክልል አሸባሪ ቡድኑ በወረራ በያዛቸዉ አካባቢዎች በንጹሃን ላይ የጅምላ ግድያ እየፈጸመ አንደሚገኝ ይታወቃል።