አንዳንድ ምዕራባዊያን ሀገራት ለአሸባሪው የህወሓት ቡድን የሚያደላ አቋም ይዘዋል

61

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 11/2014(ኢዜአ) አንዳንድ ምዕራባዊያን ሀገራት ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ለአሸባሪው የህወሓት ቡድን የሚያደላ አቋም መያዛቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም አንዳንድ የምዕራባውያን አገራት፣መንግስታትና ሚዲያዎች በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የተዛባ አመለካከት መያዛቸውን ጠቅሰዋል።

ከአውሮፓ ህብረትም ለአሸባሪው ቡድን የሚያደላ ግልፅ አቋም የሚያራምዱ መኖራቸውን የገለጹት አምባሳደር ዲና፤ የተዛባና አድሏዊ አቋማቸውን ሆን ብለው የግል ፍላጎትና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ መሆኑንም ተናግረዋል።

በመሆኑም ኢትዮጵያዊያን ጫናቸውን ከመፍራት ይልቅ በጋራ ሆነው ለአገራቸው ህልውና መቆም አለባቸው ነው ያሉት።

አምባሳደር ዲና አክልውም የግብጽና ሱዳን ሰሞኑን እያካሄዱት ያለው ወታደራዊ ልምምድ ሉአላዊ መብታቸው መሆኑንም ጠቁመው፤ "ግብጽና ሱዳን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ብቻ ሳይሆን መዋሃድም ይችላሉ፤ ቀዩ መስመር በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ከመጡ  ብቻ ነው" ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም