የአሸባሪውን ገመና የሚሸፍኑ ምእራባውያን ትንቅንቅ

81

ጥቅምት 10/2014 (ኢዜአ) አሸባሪው ህወሓት በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ከሰነዘረበት ጊዜ ጀምሮ ምእራባውያኑ ለሽብር ቡድኑ በመወገን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ጦርነት መግጠማቸውን ጋዜጠኛ አን ጋሪሰን ታስረዳለች።

ጋዜጠኛ አን ግሪሰን ምእራባውያን በተለይ አሜሪካ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እንዲህ አይነት ጦርነት ውስጥ የገባችበት ዋና ምክንያት በህዝብ ማዕበል ከስልጣን የተባረረውን ቡድን ወደ ነበረበት የአሻንጉሊት መንግስትነት ቦታው ለመመለስ ካላት ፍላጎት እንደሆነም አንስታለች፡፡

ቡድኑ በስልጣን ላይ በነበረባቸው ጊዜያት ኢትዮጵያውያንን በሀይል ቀፍድዶ ሲገዛ እንደነበር አስታውሳለች፡፡

አን ምእራባውያን ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት የገጠሙባቸው ስልቶችን ዘርዝራለች።

ከእነዚህ መካከል መሪዎችን በመተቸትና በመገናኛ ብዙሃን የተዛቡ መረጃዎችን በማሰራጨት እንዲሁም የተለያዩ ማዕቀቦችን ለመጣል ዛቻና ማስፈራሪያ በመስጠት መሆኑን ትገልጻለች።

ከዚህ በተጨማሪ እንደ አይ ኤም ኤፍ እና የዓለም ባንክ የመሳሰሉየገንዘብ ተቋማትን በመጠቀም የገንዘብ እንቅስቃሴ እንዳይደረግ በማገድ፣የተልዕኮ ጦርነት በማከናወን፣ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻዎችን በመክፈት መንግስትን ለማሸማቀቅ እያሴሩ መሆኑን ገልጻለች።

ይህን የአሜሪካን የቆየ ስልት ጦርነት ብሎ ለመጥራት የሚያስፈራ ነገር የለም የምትለው አን መሰል የጦርነት ስልቶችን ተጠቅማ በዓለም አደባባይ የታየው ውጤት ምን እንደሆነ በኢራቅ እና በአፍጋኒስታን ላይ የተከሰተውን ማየት በቂ ነው ትላለች፡፡

በቅርቡ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን የፈረሙት በኢትዮጰያ ላይ ማዕቀብ ለመጣል የሚያስችለው ሰነድ በሽብር ቡድኑ ጥቃት እየደረሰበት ያለው የፌዴራል መንግስቱ ያለ አንዳች ቅድመ-ሁኔታ መከላከሉን አቁሞ ለድርድር እንዲቀመጥ ጥሪ ማቅረቧ ልክ በሌሎቹ ሀገራት ላይ እንዳደረገችው ሁሉ የሽብር ቡድኑን ወደ ስልጣን መመለስ ላይ ትኩረት ስለማድረጓ ማሳያ እንደሆነ ጠቅሳለች፡፡

ጦርነቱን የጀመረው የሽብር ቡድኑ መሆኑ እየታወቀም ጭምር በርካቶቹ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን በዘገባዎቻቸው ሁሉ ትኩረት ሰጥተው እየዘገቡ ያሉት የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድን መንግስት መተቸት ላይ ነው ብላለች፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም