ቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በአዲስ አበባ ያስገነባው ዳቦ ፋብሪካ ተመረቀ

98

 ጥቅምት 6 2014 (ኢዜአ)  የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በአዲስ አበባ ያስገነባው በቀን አንድ ሚሊዮን ዳቦ የሚያመርት ፋብሪካ ተመረቀ።

ይሄው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተገነባው የዳቦ ፋብሪካ በቀን 1,000,000 ዳቦ የሚያመርት ሲሆን፤ ለግንባታው 217 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል።

ፋብሪካው በ6000 ካሬ መሬት ላይ የተገነባ ሲሆን፤

የዳቦ ፋብሪካ ለ450 ሰዎች የስራ ዕድል ይፈጥራል፤ በተጨማሪም በቀን 72 ቶን ዱቄት ጎን ለጎን እንደሚያመርትም ታውቋል።

በተመሳሳይ የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በቀጣይ በ10 ከተሞች የዳቦና ዱቄት ፋብሪካ ለመገንባት በሂደት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በነዚህ ከተሞችም የሚገነቡት ፋብሪካዎች እያንዳንዳቸው በቀን 400 ኩንታል ዱቄት የማምረቱ ሲሆን፤ 300,000 ዳቦ የመጋገር አቅም እንደሚኖራቸው የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት መረጃ ያሳያል።

የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በትምህርት ቤት ግንባታ ላይም እየተሳተፈ እንደሚገኝ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም