63ሺ 100 የአሜሪካን ዶላር በማዘዋወር ወንጀል የተከሰሰ ግለሰብ በእስራት እና ገንዘብ እንዲቀጣ ተወሰነበት

82

ሐረር ፤ ጥቅምት 6/ 2014 (ኢዜአ) የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት 63ሺ 100 የአሜሪካን ዶላር በማዘዋወር ወንጀል የተከሰሰን ግለሰብ በአምስት ዓመት ፅኑ እስራትና ገገንዘብ እንዲቀጣ ወሰነ።
ገብረእግዚአብሔር ሃድጉ ብሩ የተባለው ግለሰብ  ከአዲስ አበባ ወደ ጅግጅጋ ከተማ ሊያዘዋውር የነበረው የአሜሪካን ዶላር በዞኑ አወዳይ ከተማ ኬላ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ጳጉሜ 4/ 2013 ዓ. ም . እንደተገኘበት በቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ ሲጣራ መቆየቱን ፍርድ ቤቱ  ትናንት በዋለው ችሎት ላይ ተመልክቷል።

ተከሳሹም "ገንዘቡ የእኔ አይደለም ሻንጣዬ ውስጥ ማን እንደከተተው አላውቅም"  በማለት ቢከራከረም  በአቃቤ ህግ ምስክር የራሱ  የተከሳሽ መሆኑ   እንደተረጋገጠ ተገልጿል።

ፍርድ ቤቱም የተከሳሽ ተከላካይ ጠበቃ እና አቃቤ ህግ ያነሱትን የቅጣት ማቅለያ እና ማክበጃ በመመልከት ትናንት በዋለው ችሎት እጁ ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በአምስት ዓመት ፅኑ እስራት እና በ50ሺ ብር እንዲቀጣ ወስኗል።

እግዝቢትነት የተያዘው ገንዘብም በባንክ በኩል ተመንዝሮ ለመንግስት ገቢ እንዲደረግ ፍርድ  ቤቱ ወስኗል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም