የሴሬስ አፕል ጭማቂ መርዛማ ኬሚካል ስለተገኘበት ማህበረሰቡ እንዳይጠቀም መልእክት ተላለፈ

79

አዲስ አበባ፣ መስከረም 04/2014 (ኢዜአ) የሴሬስ አፕል ጭማቂ መርዛማ ኬሚካል ስለተገኘበት ማህበረሰቡ እንዳይጠቀም የኢትዮጵያ ምግብ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን አሳሰበ፡፡
ባለስልጣኑ ለኢዜአ ባለከው መግለጫ፤ የሴሬስ አፕል ጭማቂ  (Ceres apple juice) በውስጡ ሙሉ በሙሉ ለጤና ጎጅ የሆነ  ከሻጋታ የመነጨ መርዛማ ኬሚካል ተገኝቶበታል።

በመሆኑም ማህበረሰቡ ይህንን ምርት እንዳይጠቀም ሲል ባለስልጣኑ መልእክቱን አስተላልፏል።

ይህ ምርት በአለም አቀፉ የምግብ ደህንነት ማስጠንቀቂያና በአለም አቀፍ ደረጃ ጥቅም ላይ እንዳይውል መከልከሉ ተገልጿል፡፡

በዚህም የሴሬስ አፕል ጭማቂ አምራች የሆነው የደቡብ  አፍሪካ  የምግብና መጠጥ አምራች ፓየኒር ምግቦች በጭማቂው ላይ ማይኮቶክሲን የተሰኘ ከሻጋታ የሚመነጭ መርዛማ ኬሚካል ስለተገኘበት ህብረተሰቡ ምርቱን እንዳይጠቀም ማሳሰቡን በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

የጭማቂው ምርት በኢትዮጵያ ገበያ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም መክሯል፡፡

በማንኛውም አጋጣሚ ምርቱን ገበያ ላይ ካገኘ በፌዴራል ደረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8482 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት ጥቆማ እንዲሰጥ ባለስልጣኑ ጠይቋል፡፡   

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም