በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራው ልዑክ በሻሸመኔ የቦለቄ ኩታገጠም ማሳን ጎበኘ

175

ጥቅምት 4/ 2014 (ኢዜአ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራው ልዑክ በምዕራብ አርሲ ዞን በሻሸመኔ ወረዳ የቦለቄ ኩታገጠም ማሳን ጎብኝቷል፡፡

በዚህ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የቦለቄ ምርትን በማሳደግ የሀገር ውስጥ የምግብ ፍላጎትን በማሳካት ለኤክስፖርትም መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።በስፍራው የተገኙ አርሷደሮችም በሄክታር ከ30 እስከ 40 ኩንትል እንደሚያኙ ገልጸዋል፡፡

በጉብኝቱ የክልሎች ርእሳነ መስተዳድሮች እንዲሁም የአዲስ አበባና ድሬደዋ ከተማ ከንቲባዎች ተገኝተዋል፡፡