ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በአርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ በኩታ ገጠም የለማ የስንዴ ማሳን ጎበኙ

104

ጥቅምት 3/2014 (ኢዜአ) በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ የተመራ ልዑክ በአርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ በኩታ ገጠም የለማ የስንዴ ማሳ ጎብኝቷል።

በጉብኝቱም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፤ የኦሮሚያ ክልልፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ሌሎች ከፍተኛ የፌደራልና የክልል የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ በጉብኝቱ ወቅት ከዚህ በፊት የማይታረሱ መሬቶችን በማረስ በኩታ ገጠም እርሻ በስንዴ ምርት እራሳችንን ለመቻል ሰፊ ስራዎችን እየሰራን ነው ብለዋል።

በአርሲ ዞን ከታረሰው 688 ሺህ ሔክታር መሬት መካከል 388 ሺህ ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም የለማ ነው ተብሏል።

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት እንደ ሀገር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በኩታ ገጠም ማምረት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

ምንጭ-ኦቢኤን

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም