"እናንተ የአገር ተረካቢዎች ናችሁ፤ ራሳችሁን በሥነ ምግባር እና በትምህርት ማነጽ ይጠበቅባችኋል"

103

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1/2014 (ኢዜአ) "እናንተ የአገር ተረካቢዎች ናችሁ፤ ራሳችሁን በሥነ ምግባር እና በትምህርት ማነጽ ይጠበቅባችኋል" ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተማሪዎች መልእክት አስተላለፉ።

ከንቲባዋ በአዲስ ምዕራፍ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት የ2014 ዓ.ም ትምህርትን አስጀምረዋል።
ከንቲባዋ በአዲስ ምዕራፍ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ትምህርት ያስጀመሩ ሲሆን የትምህርት ቁሳቁሶች፣ ማስክ፣ ጫማ እና ሌሎች ስጦታዎችንና ለመምህራንም ገዋን አበርክተዋል።

"እናንተ የአገር ተረካቢዎች ናችሁ፤ ራሳችሁን በሥነ ምግባር እና በትምህርት ማነጽ ይጠበቅባችኋል" ሲሉም ለተማሪዎች መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

የአዲሱን ዓመት የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብር ያስጀመሩ ሲሆን ተማረዎች ውጤታማ ለመሆን በአዲስ መንፈስ፣ በመነቃቃትና ሥነ ምግባርን በመላበስ እንዲማሩ አሳስበዋል።   

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ፤ በ2014 ዓ.ም በመዲናዋ ከ910 ሺህ በላይ ተማሪዎች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።       

ተማሪዎቹ ውጤታማ የትምህርት ዘመን እንዲያሳልፉ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰው በትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ላይ ሰፊ ሥራ መሰራቱን አብራርተዋል።   

የኮሮና ቫይረስ የመማር ማስተማር ሂደቱን እንዳያስተጓጉል ለማድረግ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉንም ጠቁመዋል።

በትምህረት ቤቱ የስምንተኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ሄሜላ እዮብ ትምህርታችንን ጠንክረን ለመማር ተዘጋጅተናል ብላለች።    

ከንቲባዋ ከዚህ በፊት አጋዚያን ቁጥር 1 ይባል የነበረው ትምህርት ቤት ወደ አዲስ ምዕራፍ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት መቀየሩንም አስታውቀዋል።     

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም