የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት አባላት የሕዳሴ ግድብን ጎበኙ

121

መስከረም 30/2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት አባላት ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጎብኝተዋል።

የምክር ቤቱ ልዑክ ኑሯቸውን በለንደን ባደረጉት ኢትዮጵያዊ በአቶ አለባቸው ደሳለኝ መሪነት በአዲሱ ዓመት ዋዜማ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱ ይታወቃል።

May be an image of 1 person, standing, screen and indoor

ይህ ልዑክ ዳያስፖራው ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ በሁለንተናዊ መልኩ ማጠናከር እንዲችል ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር እየተወያየ ሲሆን በቆይታውም የተለያዩ ጉዞዎችና ጉብኝቶችን ያደርጋል።

በዚሁ መሰረት ልዑኩ የኢትዮጵያዊያን የጋራ ፕሮጀክት የሆነውን የሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር ጎብኝቱን እያደረገ ነው።

የዛሬውን ጉብኝት ያደረጉት የዳያስፖራ አባላት ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በአካል ለመጀመሪያ ጊዜ ማየት የቻሉ ናቸው። በቀጣይ የልዑኩ ቆይታ ሌሎች አባላት ፕሮጀክቱን እንደሚጎበኙ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም