የኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፍ ወጣቶች ሕብረት ለጎዳና ተዳዳሪዎች የእራት ግብዣ አደረገ

299

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፍ ሕብረት ወጣቶች በአዲስ አበባ ለሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች የእራት ግብዣ አደረገ።

ማሕበሩ ትናንት ምሽት በመስቀል አደባባይ ለጎዳና ተዳዳሪዎች የእራት ግብዣ ያደረገ ሲሆን፤ የሕክምና አገልግሎትም ሰጥቷል።

25 አባላት ያሉት ማሕበሩ በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ወጣቶች ለአገራቸው በጎ ተግባር እንዲሰሩ የሚያስተባበር ነው ተብሏል።

የማሕበሩ ፕሬዚዳንት ወጣት ቢኒያም ጌታቸው እንዳለው፤ ማሕበሩ የተቸገሩ ኢትዮጵያውያንን ማገዝ ዓላማ አድርጎ የሚሰራ ነው።

ማሕበሩ በቀጣይ በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖች በዘላቂነት የሚደገፉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚሰራ ጠቁሟል።

በመላው ዓለም ያሉ ኢትዮጵያውያን ከሚኖሩባቸው አገራት የተሻለ ልምድ ቀምረው በማምጣት በችግር ውስጥ ያሉ ወጣቶች ወደ ስራ እንዲገቡ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጥሪ አቅርቧል።

ማሕበሩ በኢትዮጵያ ቱሪዝም፣ ባህልና ቋንቋን ማስፋትና ማስተዋወቅ ላይ በስፋት እንደሚሰራ ተገልጿል።