አትሌት ሲሳይ ለማ የለንደን ማራቶን 2021 ውድድር አሸነፈ

423

መስከረም 23/2014 (ኢዜአ) አትሌት ሲሳይ ለማ ዛሬ በተካሄደው የለንደን ማራቶን የ2021 ውድድር አሸናፊ ሆኗል።

አትሌቱ በ2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከአንድ ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት ነው ያሸነፈው።

አትሌት ሞስነት ገረመው ደግሞ ሶስተኛ ሆኗል።

በተመሳሳይ በሴቶች ምድብ በተካሄደው ውድድር አትሌት ደጊቱ አዝመራው በ 2:17.58 ሁለተኛ ስትሆን እንዲሁም አሸቴ በከሪ 2:18.18 ሶስተኛ ሆነው ውድድራቸውን ጨርሰዋል።

የሴቶቹን ውድድር ኬንያዊቷ ጆሴይሊን ቼብኮስጊ አሸንፋለች።