ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ሆነው ተሾሙ

መስከረም 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ሆነው በምክር ቤቱ ተሾሙ።

ወይዘሮ ፋንታዬ ከወረዳ ጀምሮ እስከ ክልል መዋቅር ድረስ በተለያዩ የሥራ ሀላፊነት ደረጃ የሠሩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የክልሉ የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ በመሆን እያገለገሉ ነበር።

ወይዘሮ ፋንታዬ በምክር ቤት ቀርበው ቃለ መሀላ ፈጽመው ሥራቸውን ጀምረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም