አሸባሪው ህወሀት ዜጎችን በመነጣጠል ኢትዮጵያን ለማፍረስ ቢወጠንም ሴራው እየከሸፈ የህዝብ አንድነት እየጎላ መጥቷል - ኢዜአ አማርኛ
አሸባሪው ህወሀት ዜጎችን በመነጣጠል ኢትዮጵያን ለማፍረስ ቢወጠንም ሴራው እየከሸፈ የህዝብ አንድነት እየጎላ መጥቷል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 17/2014 (ኢዜአ)አሸባሪው ህወሀት ዜጎችን በመነጣጠል ኢትዮጵያን ለማፍረስ ቢወጠንም ከዕለት ዕለት ሴራው እየከሸፈ የህዝብ አንድነት እየጎላ መምጣቱን በመስቀል ደመራ በዓል የታደሙ ምዕመናን ገለጹ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ዘንድ ልዩ ስፍራ ከሚሰጣቸውና በአደባባይ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል የመስቀል ደመራ በዓል አንዱና ዋነኛው ነው።
"መስቀል የእርቅ፣ የደህንነትና የሰላም አርማና ከፈጣሪ ጋር መገናኛ ሰንሰለት ነው" ተብሎ የእምነቱ አስተምሮ ያስረዳል።
በየዓመቱ መስከረም 16 ቀን በድምቀት የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ከእምነቱ ተከታዮች ባሻገር የሌሎች እምነት ተከታዮችና የውጭ አገሮች ዜጎች የሚታደሙበት ክብረ በዓል መሆን ከጀመረ ሰነባብቷል።
ይህም በዓሉ በማይዳሰስ ቅርስነት በ2005 ዓ.ም ተመዝግቦ እንዲጠበቅና ለትውልድ እንዲተላለፍ በዩኔስኮ የተመዘገበ ሲሆን፤ ክብረ በዓሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረም ይገመኛል።
የዘንድሮው የመስቀል በዓል በአዲስ አበባ በርካታ የሃይማኖት አባቶች፣ የእምነቱ ተከታዮች፣ የውጭ አገር ዜጎችና ሌሎች ማህበረሰቦች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ በመስቀል አደባባይ ተከብሯል።
የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል አገር ችግር ውስጥ በገባችበትና "ኢትዮጵያ ትፈርሳለች" የሚል የእውሸት ፕሮፖጋንዳ እየተነዛ ባለበት ወቅት ቢሆንም ህዝቡ አንድነቱን አጉልቶና አጠንክሮ መታየቱን ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ የበዓሉ ተሳታፊዎች ይገልጻሉ።
በተለይም በአገሪቱ ሰላማዊ ምርጫ ተካሂዶ ለአዲሱ መንግስት ምስረታ ዝግጁ ሆነው እየተጠባበቁ ባለበት ወቅት መሆኑም አንሰተዋል።
አስተያየት ሰጪዎቹ አክለውም በዓሉ "አገር ትፈርሳለች" የሚለውን እሳቤ ከማፍረሱ ባሻገር ይበልጥ ኢትዮጵያዊ አንድነት ጎልቶ የታየበት መሆኑም እንዲሁ ለአገር ከሃዲዎች ምላሽ እንደሚሰጥ ነው የተናገሩት።
መስቀል አደባባይ በደማቅ ሁኔታ በተከበረው የመስቀል ደመራ በዓል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።