ኢትዮጵያን ከገጠሟት ጊዜያዊ ችግሮች ለማሻገር እጅ ለእጅ እንያያዝ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያን ከገጠሟት ጊዜያዊ ችግሮች ለማሻገር እጅ ለእጅ እንያያዝ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 17/2013 (ኢዜአ) ኢትዮጵያን ከገጠሟት ጊዜያዊ ችግሮች ለማሻገር እጅ ለእጅ ተያይዘን መዝለቅ አለብን ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የመስቀል ደመራ ታዳሚዎች ተናገሩ።
የመስቀል ደመራ በአል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ፕሬዝዳንት ሳህለወረቅ ዘውደ፣ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሰት የስራ ሃላፊዎች የአገር ወስጥና የውጭ ቱሪስቶች እንዲሁም በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት ተከብሯል።
ከእለቱ ታዳሚዎች መካከል ኢዜአ ያነጋገራቸው ዜጎች ኢትዮጵያን አሁን ከገጠማት ጊዜያዊ ችግሮች ለማሻገር እጅ ለእጅ ተያይዘን መቆም አለብን ነው ያሉት።
ያለህዝብ ተሳትፎ ስኬትና እድገት ስለማይታሰብ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት መሰረታዊ ለውጥ እንዲያመጣና የኢትዮጵያ ሰላም እውን እንዲሆን ሁላችንም ድጋፍና ትብብራችን ሊጠናከር ይገባል ብለዋል።
ከበዓሉ ታዳሚዎች መካከል ወጣት ግዛቸው ሽባባው፤ ኃይማኖታችን የሚያስተምረን ሰላምና አንድነትን በመሆኑ ለአገራችን ሰላምና አንድነት የበኩላችንን ማበርከት ይገባናል ብሏል።
ከበዓሉ ታዳሚዎች መካከል አቶ ግርማ ሲሳይ እና ወይዘሮ ትሬዛ ተስፋዬ፤ ሁላችንም ለአገራችን ቅድሚያ እንስጥ፤ አገር ከሌሌ ሁሉም ነገር የለምና ሲሉ ተናግረዋል።
የኃይማኖት አባቶችም ሆኑ ህብረተሰቡ በጋራ ለአገራቸው አንድነት በመቆም የመንግስት ጥረት ያለ ህዝብ ተሳትፎ አይሳካም እና ለኢትዮጵያ ስንል አዲሱን መንግስት ደግፈነው ልንቆም ይገባል ብለዋል።