ቀጥታ፡

"አዲስ ተሿሚዎች ለአገር የሚሰሩና ህዝብ ለማገልግል የተዘጋጁ መሆን አለባቸው"

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17/2014 (ኢዜአ) "በአዲሱ የመንግስት መዋቅር የሚሾሙ ግለሰቦች ለአገር የሚሰሩና ህዝብ ለማገልግል የተዘጋጁ መሆን አለባቸው" ሲሉ በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ አንድ የህግ ምሁር ተናገሩ።

በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ አሸናፊ የሆነው ፓርቲ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም መንግስት ይመሰርታል።

አዲስ ከሚመሰረተው መንግስት ምን ይጠበቃል ሲል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር ስመኔ ኪሮስን ኢዜአ አነጋግሯል።

አዲስ የሚመሰረተው መንግስት "የህዝብ ገዥ ሳይሆን የህዝብ አገልጋይ ለመሆን መዘጋጀት አለበት" ብለዋል።

በመንግስት መዋቅር የሚሾሙ ግለሰቦች ብቁ፣ ችሎታ  እና ራዕይ ያለቸው እንዲሁም ለአገር የሚሰሩና ህዝብ ለማገልግል የተዘጋጁ መሆን አለባቸው ነው ያሉት።

ባለፉት ሶስት አመታት የተሰሩ መልካም ጅምሮች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ያሉት ዶክተር ስመኔ፤ የተሻለ መስራት እንደሚቻል ጥሩ ማሳያ እንደነበርም ጠቅሰዋል።

በመሆኑም አዲስ የሚመሰረተው መንግስት ለኢትዮጵያ ልማትና እድገት፤ ለህዝቦች ሰላምና መረጋጋት እንድሁም አብሮነት ልዩ ትኩረት አድርጎ መስራት አለበት ብለዋል።

አንዳንደ አገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና ለመሻገር ህዝብን አስተባብሮ መስራትና የጋራ ልማትን ማምጣት ይገባልም ብለዋል።

አሁን ላይ በተለያዩ ምክንያቶች ችግር ላይ የሚገኙ ዜጎችን ማገዝና መርዳት እንዲሁም ችግሮችን በጋራ ተጋፍጦ ማለፍ ከሁላችንም ይጠበቃል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።።

የአገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ ከውጭ የሚደርሰውን ከፍተኛ ጨና መቋቋም እንደሚቻል ጠቅሰው ለዚህም ሁሉም ዜጋ የበኩሉን መወጣት አለበት ብለዋል።

መስከረም 17፤2014 (ኢዜአ)"የሚመሰረተው መንግስት የህዝብ ገዥ ሳይሆን የህዝብ አገልጋይ ሊሆን ይገባል" ሲሉ በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲት የህግ ምሁር ተናገሩ።

በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ አሸናፊ የሆነው ፓርቲ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም መንግስት ይመሰርታል።

አዲስ ከሚመሰረተው መንግስት ምን ይጠበቃል ሲል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር ስመኔ ኪሮስን ኢዜአ አነጋግሯል።

አዲስ የሚመሰረተው መንግስት "የህዝብ ገዥ ሳይሆን የህዝብ አገልጋይ ለመሆን መዘጋጀት አለበት" ብለዋል።

በመንግስት መዋቅር የሚሾሙ ግለሰቦች ብቁ፣ ችሎታ እና ራዕይ ያለቸው እንዲሁም ለአገር የሚሰሩና ህዝብ ለማገልግል የተዘጋጁ መሆን አለባቸው ነው ያሉት።

ባለፉት ሶስት አመታት የተሰሩ መልካም ጅምሮች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ያሉት ዶክተር ስመኔ፤ የተሻለ መስራት እንደሚቻል ጥሩ ማሳያ እንደነበርም ጠቅሰዋል።

በመሆኑም አዲስ የሚመሰረተው መንግስት ለኢትዮጵያ ልማትና እድገት፤ ለህዝቦች ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም አብሮነት ልዩ ትኩረት አድርጎ መስራት አለበት ብለዋል።

አንዳንድ አገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና ለመሻገር ህዝብን አስተባብሮ መስራትና የጋራ ልማትን ማምጣት ይገባልም ብለዋል።

አሁን ላይ በተለያዩ ምክንያቶች ችግር ላይ የሚገኙ ዜጎችን ማገዝና መርዳት እንዲሁም ችግሮችን በጋራ ተጋፍጦ ማለፍ ከሁላችንም ይጠበቃል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

የአገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ ከውጭ የሚደርሰውን ከፍተኛ ጫና መቋቋም እንደሚቻል ጠቅሰው ለዚህም ሁሉም ዜጋ የበኩሉን መወጣት አለበት ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም