ቀጥታ፡

የላቀ የስራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የአየር ኃይል አባላት የማእረግ እድገት ተሰጠ

መስከረም 17/2014 (ኢዜአ) የቆይታ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁ እና የላቀ የስራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የአየር ኃይል አባላት የማእረግ እድገት ተሰጠ።

የማእረግ አሰጣጥ መርሃ ግብሩም የአየር ሃይሉ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ መኮንኖች በተገኙበት ተከናውኗል።

የማእረግ እድገቱ የተሰጣቸው የቆይታ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁ እና የላቀ የስራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የአየር ሃይል አባላት ነው።

May be an image of one or more people, people standing and outdoors

የኢትዮጵያ አየር ኃይል በ1936 ዓ.ም ከተቋቋመ ጀምሮ እስካሁን የኢትዮጵያን የአየር ክልል በማስከበርና ለአገሩ ሉአላዊነት በመቆም የገዘፈ ታሪክ ያለው ተቋም መሆኑ ይታወቃል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም