ሩዋንዳ የ2025 ሮድ ወርልድ ሻምፒዮንን እንድታዘጋጅ ተመረጠች - ኢዜአ አማርኛ
ሩዋንዳ የ2025 ሮድ ወርልድ ሻምፒዮንን እንድታዘጋጅ ተመረጠች
መስከረም 16 ቀን 2014 (ኢዜአ) አለም አቀፉ የሳይክሊንግ ህብረት የ2025 ሮድ ወርልድ ሻምፒዮንን ሩዋንዳ እንድታዘጋጅ ወሰነ
ሩዋንዳ ውድድሩን እንድታዘጋጅ የተመረጠችው አለም አቀፉ የሳይክሊንግ ህብረት ይሁንታውን በመስጠቱ ነው ተብሏል፡፡
በአፍሪካ ይህን ውድድር ለማዘጋጀት ሩዋንዳ የመጀመሪያ መሆኗን ነው የቢቢሲ ዘገባ የገለፀው፡፡
የአለም አቀፉ የሳይክሊንግ ህብረት ፕሬዝዳንት ዴቪድ ላፓሪተንት “ወደ ኪጋሊ በምናደርገው ጉዞ ደስተኛ ነኝ” ብለዋል፡፡
ሩዋንዳ ውድድሩን እንድታዘጋጅ የተወሰነው በህብረቱ190ኛ ጉባኤ ላይ ሲሆን ላፓሪተንት ለሁለተኛ ጊዜ ለቀጣይ አራት አመት እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል፡፡