ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች በበርሊን ማራቶን ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከታትለው በመግባት አሸነፉ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች በበርሊን ማራቶን ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከታትለው በመግባት አሸነፉ
72
መስከረም 16 ቀን 2014 (ኢዜአ) ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች በዛሬው ዕለት በጀርመን በተካሄደው የቢኤምደብልዩ በርሊን ማራቶን ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።
አትሌት ጎይቲቶም ገብረሥላሴ በውድድሩ 2:20.09 በሆነ ሰዓት በመግባት አሸንፋለች።
ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ሕይወት ገብረኪዳን 2:21.23 በሆነ ሰዓት በመግባት ሁለተኛ ስትወጣ አትሌት ሔለን ቶላ 2:23.05 በሆነ ሰዓት ሦስተኛ ወጥታለች ።