በወንዶች የበርሊን ማራቶን ጉዬ አዶላ አሸነፈ

68

መስከረም 16 ቀን 2014 (ኢዜአ) ዛሬ በጀርመን በተካሄደው የቢኤምደብልዩ በርሊን ማራቶን አትሌት ጉዬ አዶላ በ2:05:45 በሆነ ሰአት በመግባት አሸንፏል።

በውድድሩ ኬንያዊው አትሌት ቤትዌል ዬጎን ሁለተኛ የወጣ ሲሆን በውድድሩ ተጠባቂ የነበረው አትሌት ቀኒነሳ በቀለ በሦስተኝነት አጠናቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም