የምንጓጓላትን ኢትዮጵያ ለማየት ሁሉም በተሰማራበት መስክ በተለየ ሁኔታ አስተዋጽኦ የሚያደርግበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ነን

74

መስከረም 15/2014 (ኢዜአ) "የምንጓጓላትንና በአዕምሯችን የሳልናትን ኢትዮጵያ ለማየት ሁላችንም የሚጠበቅብንን የምናደርግበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ነን" ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር ዮናስ ዘውዴ ገለጹ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር ዮናስ ዘውዴ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ ከወትሮ የተለየ ሥራ መሥራት የሚያስገድድበት እንደሆነ ገልጸዋል።  

ወቅቱ በእውቀት፣ በጉልበት፣ በጊዜ፣ በጥራት በተለየ ሁኔታ የምንከውንበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ሲሉም አክለዋል።

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ችግሩን ተረድቶ አስተዋጽኦ ካደረገ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የተሻለ ታሪክ መሥራት እንደሚቻልም አስረድተዋል።

ባለፉት ሦስት ዓመታት በርካታ በጎ ነገሮች ቢሰሩም ታሪክ የማይረሳው ኩነትም መፈጠሩን አውስተው፤ ከችግሩ ለመውጣት ሁሉም በተሰማራበት አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚገባው ጠቁመዋል።

ይህን በማድረግ "የምንፈልጋት፣ የምንጓጓላትና በአዕምሯችን የሳልናትን ኢትዮጵያ ማየት እንችላለን" ብለዋል የፍልስፍና መምህሩ ዮናስ ዘውዴ።

አገርን ለመገንባትና ወደ ብልጽግና መውሰድ የሚቻለው በእያንዳንዱ ዜጋ አስተዋጽኦ ድምር ውጤት መሆኑንም ነው የገለጹት።

አገርን በመገንባት ሂደት የተሳሳቱ አሰራሮችን አቅጣጫ በማሳየት፣ አብሮ በመሥራት፣ ችግር ፈጣሪ ባለመሆንና በሌሎች  አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም