የዓለም የቱሪዝም ቀን በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ነው

64

ሀዋሳ፣ መስከረም 14 ቀን 2014 (ኢዜአ) የዓለም የቱሪዝም ቀን ''ቱሪዝም ለሁለንተናዊ ዕድገት'' በሚል መሪ ሀሳብ ሚኒስትሮችን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ነው።

በፖሊስ ማርሽ ጣዕመ ዜማና "ቄጣላ" ታጅቦ እየተከበረ ባለው የዓለም የቱሪዝም ቀንን በማስመልከት በሀዋሳ ከተማ ሱሙዳ አደባባይ ችቦ ተለኩሷል።

በዓሉ ላይ የሲዳማ ህዝብ የተለያዩ ባህላዊ ትውፊቶች ለተመልካች ክፍት ሆነዋል።

በመርሃ ግብሩ ቱሪዝም ለሁለንተናዊ ዕድገት የሚኖረው ፋይዳና መሰል ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረጉ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።

እንዲሁም በሀዋሳ ከተማን ጨምሮ በሲዳማ ክልል የሚገኙ የተለያዩ የተፈጥሮና ባህላዊ የቱሪስት መስህብ ሥፍራዎች እንደሚጎበኙ ታውቋል።

ለሁለት  ቀናት በሚቆየው መርሃ ግብር የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከሲዳማ ክልል ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑም ተመልክቷል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም