አብዛኞቹ የሰብአዊ ዕርዳታ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ከመቀለ አልተመለሱም

142

መስከረም 6፣2014 (ኢዜአ) “የሰብዓዊ ዕርዳታ ጭነው መቀለ የገቡ አብዛኞቹ ተሽከርካሪዎች አልተመለሱም” ሲል የተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የተሽከርካሪዎቹ አለመመለስ ዕርዳታ ለተጎጂዎች የማድረስ ስራውን አስቸጋሪ እንዳደረገበትም ቢሮው አስታውቋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ ቢሮ በቲውተር ገጹ እንዳስታወቀው የዕርዳታ እህል እንዲያደርሱ 466 የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ መቀለ ቢላኩም እስካሁን የተመለሱት 38ቱ ብቻ ናቸው።

ይህ ቁጥር በዚህ ሳምንት የተላኩትን 149 ተሽከርካሪዎችን ይጨምራል።

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ተሽከርካሪዎችን ለጥፋት ተግባሩ መፈፀሚያ እያዋላቸው እንደሆነ የሚያሳዪ መረጃዎች ከሳምንታት በፊት ሲወጡ ነበር።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤትና ሰላም ሚኒስቴር የዕርዳታ እህል ጭነው ወደ መቀሌ የገቡት ተሽከርካሪዎች አለመመለስ እያሳሰባቸው እንደሆነ በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡