ዩክሬን በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር መስራት የሚያስችላትን ረቂቅ የስምምነት ሰነድ አጸደቀች

108

መስከረም 6/2014 (ኢዜአ) ዩክሬን በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መስራት የሚያስችላትን ረቂቅ የስምምነት ሰነድ ማጽደቋን ይፋ አድርጋለች።

ዩክሬን ረቂቅ የስምምነት ሰነዱን ያጸደቀችው ትላንት በነበራቸው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ መሆኑን የሀገሪቱ የዜና ወኪል ዘገባ ያመለክታል።

ረቂቅ ስምምነቱ በኢትዮጵያ እና በዩክሬን መካከል የአየር ትራንስፖርት ዘርፉን ለግል ገበያ ክፍት ማድረግን ጨምሮ በዘርፉ ቋሚእና ህጋዊ የሁለትዮሽ ማዕቀፍ እንዲኖራቸው ዕድል የሚፈጥር እንደሆነ ተነግሯል።

የዩክሬን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዩክሬንን በመወከል ሰነዱን እንዲፈርሙ እና እንዲያስፈጽሙ ለሀገሪቱ  የአቪየሽን ዘርፍ ሃላፊ ኦሌክሳንደር ቢልቹክ ሃላፊነት መስጠቱም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም