የስፖርት ማኅበረሰቡ “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ንቅናቄን ተቀላቀለ

166

መስከረም 6/2013 (ኢዜአ) የስፖርት ማኅበረሰቡ የኢትዮጵያን እውነታ ለማሳየት የተጀመረውን “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ንቅናቄን ተቀላቅሏል።

“የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” በሚል መሪ ሃሳብ የአሸባሪውን ህወሓት አገር የማፍረስ ዕቅድ የሚያጋልጥ ንቅናቄ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የንቅናቄው ዓላማ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ ላይ እያደረሰ ያለውን ጫና ለመመከት ያለመ ነው።

ይህን ተከትሎ የስፖርት ማኅበረሰቡ ዛሬ ንቅናቄውን በይፋ ተቀላቅሏል፡፡

መርኃ ግብሩን የስፖርት ኮሚሽነሩ ኤልያስ ሽኩር፣ ምክትል ኮሚሽነር ዱቤ ጅሎ እና የንቅናቄ ኮሚቴው ምክትል ጸኃፊ አክሊሉ ታደሰ በይፋ አስጀምረውታል፡፡

ታዋቂ አትሌቶች፣ እግር ኳስ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች ንቅናቄውን የሚደግፈውን ፊርማቸውን አስፍረዋል፡፡

ንቅናቄው “ኢትዮጵያ ላይ በተሳሳተ መልኩ የሚነዛው አሉባልታ ከእውነት የራቀ መሆኑን ለዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ ለማሳየት ያግዛል” ተብሏል።

በነጩ ፖስታ ጎርፍ ለነጩ ቤተ-መንግስት ንቅናቄ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ወጣቶች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

የወጣቶቹ ንቅናቄ እስከ መስከረም 15 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚቀጥል ተገልጿል።