በወሎ ግንባር በርካታ የአሸባሪው ህወሃት ታጣቂዎች እየተደመሰሱ ነው

380

አዲስ አበባ መስከረም 6/2014(ኢዜአ) በወሎ ግንባር በርካታ የአሸባሪው ህወሃት ታጣቂዎች እየተደመሰሱ እየተማረኩ ነው።

አሸባሪውን ህወሃት በመደምሰስ አኩሪ ጀብዱ እየፈጸሙ እንደሚገኙ በወሎ ግንባር የተሰለፉ የጦር መኮንኖችና የሰራዊት አባላት ተናገሩ።

በግንባሩ የጠላት መሳሪያና የአሸባሪው ታጣቂዎች እየተማረኩና እየተደመሰሱ ሲሆን ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራም እየደረሰበት መሆኑን ገልጸዋል።

የ13ኛ ክፍለ ጦር አንደኛ ሬጅመንት አዛዥ፤ ሰራዊቱ ከኃዲውንና አሸባሪውን ህወሃት በገባባቸው ሁሉ እየተከታተለ በመቅበር ላይ ነው ብለዋል።

በግንባሩ በርካታ የአሸባሪው ህወሃት ታጣቂዎች እየተደመሰሱና እጅ የሚሰጡትም እየተማረኩ ነው መሆኑን ተናግረዋል።

አሸባሪው ህወሃት በሰሜን ወሎ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ግፍና በደል በመፈፀም ላይ መሆኑን ጠቅሰው ሰራዊቱና ሌሎችም የፀጥታ ሃይሎች “ድባቅ ይመታል” ሲሉ አረጋግጠዋል።

የአገር መከላከያ ሰራዊት በተሰለፈባቸው ውጊያዎች ሁሉ በጀግንነት ጀብድ እየፈፀመና ድልን እየተጎናፀፈ መሆኑን የ13ኛ ክፍለ ጦር አንደኛ ሬጅመንት ምክትል አዛዥ ገልጸዋል።

ሰራዊቱ እያደረገ ካለው ጀግንነት በተጨማሪ ህዝቡ ከፍተኛ ድጋፍና እገዛ እያደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የአገር መከላከያ ሰራዊት በአሸባሪው ህወሃት ግፍና ስቃይ እየደረሰበት ያለውን ህዝብ ነፃ ለማውጣት መዘጋጀቱንም አረጋግጠዋል።