የፖለቲካ ፓርቲዎች ‘የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት’ ንቅናቄን ተቀላቀሉ

64

መስከረም 06 ቀን 2013 (ኢዜአ) የፖለቲካ ፓርቲዎች ‘የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት’ ንቅናቄን ተቀላቀሉ።

የኢትዮጵያን እውነታ ለመላው ዓለም በተለይም ደግሞ ለምዕራባዊያን መንግስታት ለማሳወቅና ለማስረዳት ዓላማ ያደረገ የዲኘሎማሲ አካል በሆነው በዚህ ንቅናቄ መሳተፍ አገራዊ ግዴታ መሆኑን ፓርቲዎቹ ገልጸዋል።

እንቅስቃሴው ፋይዳው የጎላ መሆኑን የገለፁት ፓርቲዎቹ፤ የምዕራባውያን ሚዲያ የተዛባ ዘገባ አንዳንድ አገራት የተሳሳተ አቋም እንዲወስዱ እንዳደረጋቸው ጠቅሰዋል።

በዚህም አገራቱ ኢትዮጵያ ላይ እያደረሱ ያለውን ጫና ለመቀልበስ ንቅናቄው እንደሚረዳ አመልክተዋል።

‘የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት’ ዘመቻ የኢትዮጵያን እውነተኛ መረጃ በመግለጽ የአሸባሪውን ህወሓት አገር የማፍረስ ሴራ ለሌላው ዓለም ለማሳወቅ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርም ተፎካካሪ ፓርቲዎቹ ገልጸዋል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ አቶ ማሙሸት አማረ፣ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ አቶ ሙሳ አደም እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶክተር ራሄል ባፌ ተገኝተው ወደ ነጩ ቤተመንግስት የሚላከው ደብዳቤ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል።

‘የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግሥት’ በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለው አገር አቀፍ ዘመቻ እስከ መስከረም 15 ቀን 2014 ዓ.ም የሚቀጥል ሲሆን በኢትዮጵያ ዩዝ ኢምፓወርመንት ማኅበርና አገር አቀፍ የወጣቶች ንቅናቄ የተዘጋጀ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም