የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ከ4 ሺህ በላይ ተማሪዎችን የፊታችን ቅዳሜ ያስመርቃል

163

አምቦ መስከረም 6/2014 (ኢዜአ) የአምቦ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ሙያዎች ያሰለጠናቸውን ከ4 ሺህ በላይ ተማሪዎች የፊታችን ቅዳሜ ለማስመረቅ መዘጋጀቱን አስታወቀ።

የዩኒቨርሲቲው ዓለም አቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ዶክተር መንግስቱ ቱሉ ለኢዜአ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው በመደበኛና ተከታታይ መርሀ ግብር በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 4ሺህ 900 ተማሪዎች ለማስመረቅ ተዘጋጅቷል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 1ሺህ 980 የሚሆኑት ሴቶች  መሆናቸውን ተናግረዋል

የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና መምህራን ፣ የተመራቂ ቤተሰቦችና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት የምረቃ ስነ ስርአቱን ለማካሄድ ዝግጅት መደረጉን ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።