የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም ይሰጣል

364

መስከረም 5/2013 (ኢዜአ) የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2014 የሚሰጥ መሆኑን አገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ አስታወቀ።

የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ፤ የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም ይሰጣል ብለዋል።

የመፈተኛ ወይም የአድሚሽን ካርድ ከመስከረም 24 እስከ 26 ቀን 2014 ዓ.ም ለተማሪዎች እንደሚሰጥም ገልፀዋል።

ከ618 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀመጡ የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ ለዚህም ፈተኝ መምህራንን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን በማሟላት በቂ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።