በምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሚመራ የልዑካን ቡድን በአፋር ክልል በአሸባሪው ሕወሓት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ሰመራ ከተማ ገባ

185

መስከረም 5/2014 (ኢዜአ)በአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሚመራ የልዑካን ቡድን በአፋር ክልል በአሸባሪው ሕወሓት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ሰመራ ከተማ ገብቷል።

ልዑካን ቡድኑ ሰመራ ሱልጣን አሊሚራህ ሀንፍሬ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የአፋር ክልል ርእሰ መሥተዳድር አወል አርባ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገዋል።

በአሸባሪው ሕወሓት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ሰመራ ከገባው ልዑካን ቡድን ጋር የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ባለሀብቶችን እና የንግዱን ማኅበረሰብ ተገኝተዋል።ምንጭ-ከአዲስ አበባ ፕረስ ሴክሬታሪያት