ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ለፋና ሁለገብ አካል ጉዳተኞች ማህበር የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

መስከረም 4/2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ለፋና ሁለገብ አካል ጉዳተኞች ማህበር ለኮቪድ መከላከያ የሚያገለግሉ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ድጋፉን ያደረገው ማህበሩን በጎበኘበት ወቅት ነው።

በኢንስቲትዩት የንብረት አስተዳደር እና የጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ሰለሞን ለማ፤ ኢንስቲትዩቱ ለማህበሩ ማስክ፣ ሳኒታይዘር፣ ፈሳሽ ሳሙና እና የሶፍት ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ለማህበሩ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው፤ በቀጣይም በጨርቃ ጨርቅ ሙያ ዘርፍ መሰልጠን ለሚፈልጉ የማህበሩ አባላት ሥልጠና ለማዘጋጀት ቃል ገብተዋል።

የፋና ሁለገብ አካል ጉዳተኞች ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ካህሳይ ዘገየ በበኩላቸው፤ ኢንስቲትዩቱ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ፋና ሁለገብ አካል ጉዳተኞች ማህበር 257 አባላት አሉት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም